ይመጣል ጌታችን!!
“እናንተ የገሊላ ሰዎች ስለምን
ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ቆማችኋል?
ይህ ወደሰማይ ሲያርግ ያያችሁት
ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲያርግ ባያችሁት
ዓይነት ተመልሶ ይመጣል” አሉአቸው።
የሐዋርያት ሥራ 1 ፡ 11
እኛኑን ሊያድነን ከሰማይ ቢመጣ
ከአዳም ዘር ከማርያም ብቻ ስለወጣ
አለቃ ነው ሲባል ደግሞም ጌትነቱን
ስላልተቀበሉት የአምላክ ልጅነቱን
አሰወግደው ብለው ፈረዱበት ሞትን
እንደወንጀለኛ በመስቀል ሰቀሉት
የሚይዘው መስሎአቸው ማህተም አተሙት
መቃብር እንደማይችለው ፍጹም አልተረዱት
በሶስተኛው ዕለት ሳያስቡት ድንገት
ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ በጠዋት
ከሞት ከተነሳ አርባ ቀን ቆይቶ
ለደቀመዛሙርቱ ሁሉን አስረድቶ
የጠፉትን ሁሉ ወደ እውነት መልሶ
ጊዜው ሰዓቱ ሲደርስ ሄደ ተመልሶ
ይመጣል ጌታችን በወሰነው ሰዓት
ቤትን አዘጋጅቶ ለዘለዓለም ሕይወት
ለጻድቃን ትንሳኤ ለኃጢያተኞች ሞትን
ይመጣል ጌታችን ለመወሰን ይህንን
በጌታዬ መምጣት እኔ ተስማምቼ
የዓለም ቅራቅንቦ ወደኋላ ትቼ
ራሴን በመናቅ ንስሐ ገብቼ
እየጠበቅሁ ነው እህት ወንድሞቼ
ምንስ አሰባችሁ ምንስ ተሰማችሁ
ጌታችን ሲመጣ ምንድነው ፍርዳችሁ
በግራ ነው በቀኝ እርሱ የሚያቆማችሁ
ይመጣል ጌታችን እኛኑን ሊወስደን
ለምንጠብቀው በኢየሱስ ተማምነን
በቸር ይግጠመን!!
ኃይሉ ነኝ!
No comments:
Post a Comment