እግዘኣብሔር
ከጥንቱ የተናገረለት፤
ኢሳያስ ሚክያስ የተነበዩለት፤
ዳዊት በውዳሴ ለእርሱ የገለፀለት ፤
ዮሐንስ ጎዳና ጠርጎ ያዘጋጀለት፤
የምሥራቹን ቃል
ሱራፌል መላእክት
ተወልዶአል ብለው የመሠከሩለት፡፡
ልዑል የእግዚኣብሔር ልጅ
መሲህ የዓለም ወዳጅ
ተወልዶአል አማላጅ፡፡
ገና ጥንት ከዘመናት
በፊት
እግዚኣብሔር
ለዳዊት ቃል እንደገባለት
ጦረኛ ስለሆንክ ስላለ በእጅህ
ደም
ቤቴን ልትሰራ አንተ አትችልም
ቤቴን የሚሰራው ከአብራክህ የሚወጣው
ያንተ ልጅ ብቻ ነው
ከአብራክህ የሚወጣው
አንተ የምትወልደው
ልዑል የእግዚኣብሔር
ልጅ ተብሎ ሚጠራው
ዙፋኑ ዘለዓለም የማይናወጥ ነው
የሰው ልጅ አዳኝ ነው
ከአንተ የሚገኘው፡፡
ስለእርሱ የገለፀው ነቢዩ ሚክያስም
አንቺ ቤተልሄም ታናሽ ብትሆኝም
ከቁጥር ባትገቢም ሰው
ባያስብሽም
የእስራኤል ገዥ ከአንቺ ይወለዳል
የእግዚኣብሔር ክብር በአንቺ ይገለፃል፡፡
ከብዙ ዓመታት ከዘመናት
በፊት
እንደተናገረው ኢሳያስ
በትንቢት
እነሆ ድንግል ልጅን ታረግዛለች
ወን ድ ልጅም ደግሞ እርሷ ትወልዳለች
ስሙን አማኑኤል ብላ
ትለዋለች
የእግዚኣብሔር ክብር በእርሱ ይገለፃል
ሰው ሁሉ በአንድነት ልዑሉን ያዩታል፡፡
አዳምና ሄዋን በገነት ውስጥ ሳሉ
የተከለከለውን በለስ ስለበሉ
ኃጢያትን በደልን በመፈፀማቸው
አትብሉ ተብለው ያን በመብላታቸው
ልዕል እግዚኣብሔርን በማሳዘናቸው
ሁለተኛ ጥፋት እንዳይገኝባቸው
ከገነት አባሮ በሩን ዘጋባቸው
በአዳም ምክንያት ደግሞም በበደሉ
አዳምና ሄዋን ፍጥረታት በሙሉ
ከእርግማን በታች ሁሉም
በመዋሉ
እግዚኣብሔር አምላክም ይህንን በመመልከት
ሊያድነው ፈለገ ከተፈረደበት
ፍጥረት እንዲሻገር ከሞት ወደ ሕይወት
በዋኔስ ሞከረ አልተሳካለትም
ከሞት ወደ ሕይወት አልተሸጋገረም
ባደረገው በጎ ከመሞት አልዳነም
በጥቦት ባውራ በግ
በፍፁም አልሆነም
በሁሉም ሙከራ ሰው ነጻ አልወጣም፡፡
ስለዚህ መፍትሔው የአዳም መዳኛው
ልጁን ላለም ፍጥረት
በመስጠት ብቻ ነው፡፡
ስዓትና ጊዜ ዕለታቱ ሲደርስ
የአዳም ዘሪያ ከሞት ለመመለስ
ተወለደ ልዑል አዳኝ
የእግዚኣብሔር ልጅ
የፍጥረታት ጌታ የሰው ልጅ አማላጅ፣፣
ሰባ ሰገሎች የምድር ጠቢባን
የተነገረው ቃል ተግባራዊ እንዲሆን
ከምሥራቅ ተነስተው
በኮከቡ ምሪት
ቤተልሔም ድረስ እሱ እስካለበት
ዕጣንና ከርቤ ወርቅ አልማዝ
ስጦታ
ይዘው መጥተውለት ለሕፃኑ
ለጌታ
በእግሩ ሥር ሰገዱ ተገቢውን ሰላምታ፣፣
ተወለደ ልዑል ተወለደልን
ከኃጢያትና ከሞት
እኛኑን ሊያድን
በአነስተኛ ሥፍራ
እርሱ የተወለደው
ልዑሉ ተዋርዶ እኛን
ሊያከብር ነው፣፣
ታዲያ?
የእግዚኣብሔር
ልጅ በልብህ ተውልዶአል?
ልዑሉን በልብህ ሥፍራ ሰጥተህዋል?
በእርግጥ
በአዳኝነት ተቀብለህዋል?
ወይስ በዘልማድ
ጉዞ ጀምረሃል!!
ልዑል በሕይወትህ ሊወለድ
ይገባል።
በቸር ይግጠመን!!
ኃይሉ ነኝ Dec 24/2008.
No comments:
Post a Comment