ጌታ ሆይ ቶሎ
ና!!
ደቀመዛሙርቱ
ብቻቸውን ወደ እርሱ ቀርበው
“ይህ
ሁሉ ነገር የሚሆነው መቼ ነው ?የመምጫህና
የዘመኑ
መጨረሻ ምልክትስ ምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት
ማቴዎስ 24፡3
የትንቢት አዋጆች ሁሉም ተፈጽሞአል
የመጨረሻው
ዘመን በፊታችን ሆኖአል
የጎርፍ
ሙላቱ የምድር ሙቀቱ
በነዚህ
ምክንያት የሰው ልጅ ቅስፈቱ
የዓለም
መናወጡ በየስፍራው ጥፋት
አንደኛው
በአንዱ ላይ በጦር መነሳሳት
እዚያም
እዚህም ወንጌል ይሰበካል
የዳነው
ድኖአል ያልዳነው አምጾአል
አመጸኛው
ደግሞ ወንጌሉን አጣሞአል
ለራሱ
አምላኩ እኔ ነኝ ብሎአል
መጭው
ክርስቶስን በራሱ መስሎአል
አምላክ
ተብሎ ይሰገድለታል ይመለክለታል
በዓለም
በምድራችን ደግሞም በአህጉራችን
የሀሰት
ክርስቶሶች ሲፈሉ እንደአሸን
ሰማን
በጆሮአችን አየን በዓይኛችን
በየአደባባዩ
በተቀደሰ ሥፍራ
ስለአምላክ
ነገር አንድም ሳይፈራ
ርኩሰት
በዝቶአል ድሪያ አመንዝራ
ዘመኑ
ከፍቶአል ለእህምሮ ይከብዳል
የእግዚኣብሔርን
ትህዛዝ ሕጉን አቃለዋል
አምላክን
በመናቅ ይጋባል ያጋባል
ሁኔታውን
ሁሉ ስንመረመር ሚስጢሩን
የክርስቶስ
ኢየሱስ መምጫው መቃረቡን
በዚህ
ይታወቃል በጫፍ ላይ እንዳለን
ዘመኑ
የሰላም ነው እየተባለ ሲባል
ድርቅና
ቸነፈር ምድርን አስቸግሮአል
የአውሎ
ንፋሱ ዓለምን ሲያስጨንቀው
በደጅ
እንደቀረብክ ምልክቱ ይህ ነው
ያለመተማመን
ደግሞም መከዳዳት
የበሉትን
በልተው እርስ በእርስ መጠፋፋት
ጌታ ሆይ!!
ይመስላል የምትመጣበት ሰዓት
ወንጌል
ተነግሮአል ትንቢቱም ተፈጽሞአል
በቃልህ
እንዳዘዝከን ዓለምን ዞረናል
ትህዛዛትህንም
ሁሉ ፈጽመናል
የመምጣትህ
ነገር በጣሙን ናፍቀናል
ማራናታ
እያልን በፊትህ እንጮሃለን
ጌታ ሆይ!
ቶሎ ና እኛም እናርፋለን።
በቸር ይግጠመን!!
ኃይሉ ነኝ! Feb,2013
No comments:
Post a Comment