አዲስ ነገር ይሆናል
በሰላሳኛው ዓመት በአራተኛው ወር
የአይሁድ ምርኮኞች እያሉ በኬባር
የተነገረው ቃል በተግባር እንዲውል
ብዬ የምናገር እግዚር እንዲህ ይላል
እኔ የቡዚ ልጅ የሆንኩት ሕዝቅኤል
ንጉሥ ኢኮንያን በተማረከበት
በአምስተኛው ዓመት በአምስተኛው ዕለት
በኬባር ሸለቆ ባለሁበት ሰዓት
የእግዚኣብሔርን መንፈስ ከሰማየ ሰማያት
በክብሩ እንዳለ እግዜርን አየሁት
የእግዚኣብሔር መንፈስ በእቅፉ እንደያዘኝ
እጅግ የደረቁ ብዙ አጥንት አሳየኝ
በተከማቹበት ሸለቆ አኖረኝ
እንደዚህ በማለት ጥያቄ ጠየቀኝ
እነዚህ አጥንቶች ሞተው የደረቁት
በዚህ ሸለቆ ውስጥ ተከማችተው ያሉት
ዳግመኛ የሚያገኙ ይመስልሃል ሕይወት ?
ይህንን ጥያቄ እግዜር ሲጠይቀኝ
እንደዚህ ነበረ መልሴን የሰጠሁኝ
አንተ ታውቀዋለህ እኔ ምን አውቃለው
ገሎ የሚያድን ካንተ ሌላ ማነው?
እግዚኣብሔር አምላክም ቃል እየነገረኝ
ለእነዚህ አጥንቶች እንደዚህ በል አለኝ
እኔም በታዘዝኩት ትንቢት ተናገርኩኝ
መናገር ስጀምር ኮሽኮታ ሰማሁኝ
አጥንት ከአጥንት ጋር ሲያያዝ አየሁኝ
እጥንት በጅማት በሥጋ ሲሸፈን
በቆዳ ሲለበጥ
ሙሉ አካል ሲሆን
ይህ ተፈጸመ እግዚኣብሔር ሲወስን
ቀጥሎም እንዲህ አለኝ
እግዚር ተናገረኝ
አካል ሙሉ እንዲሆን ያሻዋል እስትንፋስ
በአራቱም ማዕዘናት ተናገር ለንፋስ
ደግሞም በታዘዝኩት ትህዛዝ መሰረት
ንፋስ ግባ ብዬ ስናገረው ትንቢት
ሕይወት የሌላችው ተጋድመው የነበሩት
እስትንፋስ አግኝተው ሆኑ እንደሰራዊት
ዘመን አልፎልን ሲመጣ ዘመን
ድንቅን አይተናል በደግ አምላካችን
ሳምንት በሳምንት በወር
በዓመታት
ጌታ ሰጥቶናል ብዙ በረከት
በያዝነው ዓመት በምንጠብቀው
የእግዚኣብሔር ሥራ እኛ የምንሰራው
መሥራት ያለብን እኛ ያልሰራነው
ሥራውን ሊሰራ ሊያስተካክለው
የጌታችን ፈቃድ ዓላማው ያ ነው
በአዲሱ ዓመት አዲስ ነገርን
ያደርጋል ጌታ ውድ አምላካችን
በቸር ይግጠመን!!!
ኃይሉ ነኝ! Jan2009
No comments:
Post a Comment