ጌታዬን
መረጥኩት
ዘመኔን በሙሉ በዓለም
ስመካ
የሚሆንልኝ መስሎኝ
ሕይወቴ የሚረካ
በዘመድ አዝማዴ በዘር
ማንዘሮቼ
የምኖር ሲመስለኝ በምኞት
ተስማምቼ
ረጅሙን ዘመኔን ያለፈው
ሕይወቴ
ዓለም በምትሰጠው ከንቱ
በመመካቴ
መስለውኝ መሰረቴ የሕይወቴ
አለኝታ
ለእኔ ስመራርጥ የሚሆነኝ መከታ
እጄን ስዘረጋ ለማግኘት
ዕርዳታ
ሁሉም ብንን አሉ አልተገኙም
ላፍታ
የወደዱኝ መስለው ዘላለም
የሚኖሩ
ወደማይቀረው ዓለም
ወደዚያ ሲያመሩ
ለብቻችን ስንቀር እኔና
ብቸኝነት
እጓጓ ነበረ እረዳት
ለማግኘት
በውስጤ ሰላም የለኝ
እኔን የሚያጽናናኝ
በዙሪያዬ ደግሞ ሰላም
የሚሰጠኝ
ለማርካት ሳመቻች የልቤን
ፍላጎት
ጌታ ኢየሱሴን ድንገት
አገኘሁት
ሕይወቴ ተቀይሮ ጌታን
ተቀበልኩት
እሱ እንደመረጠኝ ጌታዬን
መረጥኩት።
በቸር ይግጠመን!!
ኃይሉ ነኝ!
No comments:
Post a Comment