ጽጌረዳ
ጽጌረዳ የአበባ
ውብ
ከሩቅ ወደእሷ
የምትስብ
ሮዝ ቀይ ጃኖ
ለብሳ
በአጋም መካከል
ተኮፍሳ
ወደ እርሷ
ልጠጋ ወድጄ
ልዳስሳት ልነካት
በእጄ
መስሎኝ ሳያት
፤ እሾህ ያላት
ብዙ ራቅኳት
፤ ተለየኋት
ጽጌረዳ ጣፋጭ
ስዊት
የአበቦች ዓለም ንግሥት
ውብ መዓዛ
ያላት ለዛ
ዘመን የሚያመጣውን
አይቼ
ከዘመን ጋር
የሚሄደውን ሸኝቼ
የጀርባዬን
እኔነቴን ተመልክቼ
ቁጭ ብዬ ባለሁበት
ሰዓት ተዝናንቼ
በአበባ መካከል
ቁጭ ብላ
ከፊት ከኋላ
ኖሯት ከለላ
ፅጌረዳን አየኋት
አገኘኋት
እንዳልርቃት
ከአደይ አበባዬ ጋር ናት
እንዳልተዋት
እንዳልረሳት ታስጎመጃለች
ፍሬ አላት
አበባ ነች
ራስዋን ቀና
አድርጋ
ፅጌ ረዳ ሆና
የበጋ
ፈገግታዋን
እያሳየች
እንዲህ አለች
ትወስደኛለህ
!!?? አለች
አትወስደኝም
ዳግም ተናገረች
እንደ ውዳሴ
ማርያም እየደገመች
የማልሸኛት
እርሷ መስሎአት
እኔም አልኳት
ልቤም አላት
የውስጤን የልቤን
ነገርኳት
አንቺን ያልወሰድኩሽ
የልቤ የውስጤ
ያላደርግኩሽ
ፅጌረዳዬ ብዬሽ
ከአበቦቼ መካከል
አስቀምጪሽ
ጠዋት ማታ
ታቅፌሽ
በአደባባዬ
ተክዬሽ
ለፍሬ ለአበባነት
አድርሼሽ
ለቤቴ ውበት
ሰጥተሽ
የእኔ የራሴ
አድርጌሽ
እኖራለሁ ከአንቺጋር
ውበትሽ ሳይከስም
በክብር
ይህንን ገልጪ
ብነግራት
እኔ ቋንቋ
አላውቅም በማለት
እየጣረች ነው
እንዳልወስዳት
በምን ቋንቋ
ላስረዳት
የመውሰድ ትርጉሙን
ትጠይቃለች
እያስረዳች
፤ ግን ትሰነጣጥቀዋለች
እንጨት ይመስል
ትፈልጣለች
ፊደል ቋንቋውን
ትናገራለች
ከፋ ይሁን
ሔረርጎታ
ምናልባትም
አሳይታ
የበቀለችበት
ቦታ
ቤተልሔም ይሁን
ናዝሬት
ፊደል ሐዋርያ
የቆጠረችበት
እኔ ከቋንቋ
ምን አለኝ
ከቀዬ ምን
ሊተርፈኝ
እኔ የምፈልገው
ፅጌረዳነት
ከምትሰጠው
መሀዛ ውበት
ፅጌረዳዬን
በአበባዬ መካከል አድርጌአት
በዓይኔ ሸኘዋት
አደረስኳት
እንዳለችው
አልወሰድኳት
በእቅፌ አላደረግኳት
ልቤ ግን ተከተላት
ከአበቦች መንደር አደረሳት
ብቻ ብቻ ልቤ
ተረዳት
ውሰደኝ ካለች
ልውሰዳት
በቸር ይግጠመን!!!
ኃይሉ ነኝ August 12/2006
No comments:
Post a Comment