ፍቅራችሁ
ያለግብዝነት ይሁን!!
ይህ ዓረፍተ ነገር የተገለጸው በሮሜ መጽሐፍ ሐዋርያው ጳውሎስ ለሮሜ
ሰዎች በጻፈው መልእክት ውስጥ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ሊያስረዳቸው የፈለገው ፍቅራችሁ እርስ በርሳችሁ፤አንዱ ለአንደኛው የሚወድበት
ፍቅር እውነተኛ ፍቅር ይሁን ለማለት ነው። ያ ፍቅር ያለግብዝነት ይሁን ይላል ። ግብዝነት ምንድን ነው? ሳባ የአማርኛ መዝገበ
ቃላት እንዲህ ይላል “ለራሱ የሚያደላ ፤ ይሉኝታ ቢስ ፤ ሰነፍ ሲለው ፤የከሳቴ ብርሃን ተሰማ መዝገበ ቃላት ደግሞ ቁም ነገር የሌለው
ይላል። ጌታ ኢየሱስ ደግሞ እኔ እንደወደድኳችሁ እርስ በራሳችሁ ተዋደዱ ብሎ ሕግ ደንግጎ አስቀምጦልናል። ጌታ ኢየሱስ በምን ዓይነት
ፍቅር ወደደን? በግሪክ ቋንቋ ፍቅርን በሶስት ዓይነት መድበውታል ወይም ለሶስት ዓይነት የተለያየ ፍቅር ሶስት የተለያየ ስም ሰጥተውታል።
ኤሮስ ፤ ፊሊያ ፤ አጋፔ ግሪካውያን ሁለቱን ለተለያየ የፍቅር ዓይነት ሲጠቀሙበት ፤ አጋፔን ግን ለእውነተኛ ፍቅር እግዚኣብሔር
የሰውን ልጆች የወደደበትን ፍቅር ለመግለጽ ይጠቀሙበታል። “ዓለምን እጅግ ስለወደደ፤ አንዲያ ልጁን ሰጠ በዮሐንስ 3፡16 እንደተገለጸው
እጅግ ስለወደደ ይላል ። እጅግ ለምትለው ቅጽል ቃል የከሰቴ ብርሃን መዝገበ ቃላት “እጅግ የበዛ፤ ውስጠ ብዙ ልክ የሌለው ። አደገ፥
በዛ ክልክ ዐለፈ ብሎ ያፍታታዋል።እግዚኣብሔር ከልክ ባለፈ ልክ በሌለው ፍቅር ነው የወደደን ማለት ነው ። እግዚኣብሔር አንዲያ
ልጁን ጌታ ኢየሱስን በመስቀል እስኪሞት ድረስ ያሳየን ፍቅር ነው ግሪኮች አጋፔ የሚሉት፤ ጌታ ኢየሱስም እኔ እንደወደድኳችሁ እርስ
በርሳችሁ ተዋደዱ ሲል ከልክ ባለፈ ፍቅር እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ነው ምሳሌ አድርጎ ራሱን ያቀረበው። ጌታ ኢየሱስ እርስ
በእርሳችሁ ተዋደዱ ብሎ አላቆመም። ወንድማችሁን እንደምትወዱ ጠላታችሁንም ውደዱ ብሎአል። ፍቅር እውነተኛ ሆኖ የሚገለጸው ወንድምን
እንደራስ ሲወዱ ነው ። አደባባይ ላይ ፍቅርን በተከሸነ ቃላት መግለጽ ይቻላል ፤ ወንድሜ! ወንድሜ! እያሉም ጉንጭና ትክሻን በመሳም
ለታይታ ልናደርገው እንችላለን ። ግን ያ አይደለም ዋናው ነጥብ ወንድሜንና እህቴን በእውነተኛው ፍቅር፤እንደራሴ ወድጃአለሁ ነው።በሉቃስ
ወንጌል ምዕራፍ 10 ላይ ስለደጉ ሳምራዊ ጌታ ኢየሱስ ያስተማረው ምሳሌ አንዳንዶቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ ተምረነዋል እናውቀዋለን።
አንድ ሰው ወንበዴ አግኝቶ እንደበደበውና ፤ካህኑ በእግዚኣብሔር ቤት የሚያገለግለው ቅዱስ ነን ፤እኛ የእግዚኣብሔር ምርጦች ነን
፤ አንዳችም ኃጢያት የለብንም ከሚሉት አንዱ በዚያ በኩል ሲያልፍ
አይቶ እንዳላየ አለፈ ፤የሲቃ ጩኽቱ ወደልቡ ሊደርስ አልቻለም ። እንባው አልተሰማውም አለፈ መንገዱን ቀጠለ። ቀጥሎ
በእግዚኣብሔር ቤተ መቅደስ ዕጣን የሚያጥነው ሌዋዊ እርሱም በዚያ ሲያልፍ የድረሱልኝ ድምፅ ወደ ጆሮው ገባች፤ ዓይኑን አሻቅቦ ቢያይ
በደም የተበከለና መሐል መንገድ ላይ የተጋደመ ሰው መሆኑን ተረዳ ዓይኑን ጨፍኖ መንገዱን ነጎደ። አንድ ሳምራዊ ግን አነስተኛ ምናምንቴ
የሆነው በዚያ በኩል ሲያልፍ ሞትኩኝ ድረሱልኝ የሚል ለቅሶ ሰማ ይህ ሰው መሆን አለበት ማየት አለብኝ ብሎ ተጠጋው ሲያየው ወንበዴዎች
እንዳይሞት እንዳይሽር አድርገው የደበደቡት ምስኪን መሆኑን ተረዳ፤ ገንዘቡ፤ የሚጓጓዝበት አህያ ተወስዶበታል። የለበሰው ልብስ እንኳን
ሳይቀር የለም ወንበዴዎቹ ወስደውታል። መጀመሪያ ሳይጸየፈው ደሙን ጠርጎ በዘይትና በወይን ጠጅ ቁስሎቹን ጠግኖለት በፋሻ አሰረለት።
የራሱን አህያ ሰጥቶት ። ወደእንግዶች ማደሪያ ቤት ወሰደው ፤ እዚያም የሚገባውን ከፍሎ በሆቴል ቤት ውስጥ እንዲያርፍ አደረገ ፤በስተመጨረሻም
ሁለት ዲናር ከፍሎለት እስኪያገግም በእንግዶች ማረፊያ እንዲቆይ አደረገ ያ ብቻ አይደለም ተጨማሪ ወጪ ቢኖርበት እንደሚከፍል አረጋግጦ
። ወደ ሚሄድበት ሄደ። ጌታ ኢየሱስ ለሰውዬ እንደጠየቀው እኛም ራሳችንን ልንጠይቅ ይገባናል ለወንድሜ ምን ያህል ፍቅር አለኝ?
የተራበውን ወንድሜን ወደቤቴ ግባ እሳትም ሙቅ ብለው ምን ይጠቅመዋል አይደል ያለው የእግዚኣብሔር ቃል። በእርግጥ ወንድሜን እንደራሴ
እወደዋለሁ? ዋናው ጥያቄ ይህ ሲሆን መልስ ልንመልሰው የሚገባ ነው ። ወንድሜን እንደራሴ ካልወደድኩት ራሱ ግብዝነት ነው ግብዝነት
ደግሞ እንደጌታ ኢየሱስ ትህዛዝ ወንድሜን አልወደድኩትም ማለት ነው ። ጌታ ሲመጣ እናንተ ያባቴ ብሩካን ልንባል እንፈልጋለን!!
ወንድሜንና እህቴን በእውነተኛ ፍቅር ልንወዳቸው ይገባል!!።
ቸር ይግጠመን!!
ኃይሉ ነኝ!!
No comments:
Post a Comment