አልከዳህም!!! ትከዳለህ
ኢየሱስም፤ “ በእውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ በዚህች ሌሊት ዶሮ
ሁለት ጊዜ ከመጮኹ በፊት አንተ ሦስት ጊዜ ትከዳኛለህ”
አለው። ማርቆስ 14 ፡ 30
አይሁድ ተሰብስበው ጌታችን
ሊሰቅሉት
በመጨረሻው ዕለት በቀረችው
ሰዓት
እግራቸውን አጥቦ ሲያበላቸው
እራት
ቁጭ ብለው ሳለ በሰው
ቤት ሰገነት
ከመውጣታቸው በፊት ወደ
ደብረ ዘይት
ለተከታዮቹ ለደቀመዛሙርት
ጌታ እንዲህ አላቸው
እረኛው ሲመታ ይበተናል
መንጋው
ችግሩ ሲመጣ ሁሉም ይከዳኛል
ከእናንተ እያንዳንዱ
እኔን ይረሳኛል
ጴጥሮስ እንዲህ አለ
እኔ አልለይህም
እስከ ሞትም ድረስ ፍጹም
አልከዳህም
ሁሉም ቢከዳህም እኔ
አልተውህም
ጴጥሮስ አትሳሳት አትናገር
ውሸት
ሶስቴ ትከዳለህ ዶሮ
ሳይጮኽ ሌሊት
ጌታችን ሲገርፉት በመቃ
ሲመቱት
በጃኖ ሸፍነው ማን መታ
እያሉት
እንደ ሰው ቆጥረውት
ሲያላግጡበት
ፍዳውን ሲያበሉት ይህንን
በመመልከት
ይከተለው ጀመር ሆኖ
ከእርሱ በርቀት
ጴጥሮስ ርቆ ሄደ ሰዎችን
በመፍራት
ካህናት ግቢ ውስጥ በትችኛው
በኩል
እሳት በሚሞቁ በስዎች
መካከል
በየፊናው ሥራውን ሲተገብር
ጴጥሮስ በበኩሉ በፍርሓት
ላይ ነበር
ከገረዲቱ አንዱ ወደ
እርሱ ተጠግታ
በእርግጥ ስላወቀችው
በጣም ተመልክታ
አንተ ከናዝሬቱ ጻድቅ
ከምትለው
ከኢየሱስ ጋር ነበርክ
ብላ ስትለው
አንቺ የምትይው አላውቅም
ያንን ሰው
ሆኖ በመደንገጥ ሀፍረት
እየገባው
ለመጀመሪያ ጊዜ ድንገት
ሳያስበው
ጌታውን በመክዳት ሄደ
ወደ መግቢያው
በዚያ ሰዓት ነበር ዶሮ
ሊጮኽው የቻለው
ከሰዓት በኋላ በዚያ
ስፍራ ላሉት
በበሩ አቅጣጫ ቆመው
ለሚገኙት
ይህ ሰው ከነርሱ ጋር
ነበረ በማለት
ስለተናገረች በዚያ ለነበሩት
ይህ የምትይው የምትናገሪው
አላስታውሰውም
እኔ ከእርሱ ወገን ፍጹም
አይደለሁም
ለሁለተኛ ጊዜ ሆኖ በሰዎች
ፊት
መዋሸት ጀመረ ጌታውን
በመክዳት
ለሶስተኛ ጊዜ በዚያ
የተሰበሰቡት
ክብ ዙሪያ ቆመው እሳት
ለሚሞቁት
አንተ የገሊላ ሰው እንደመሆንህ
መጠን
አንጠራጠርም ከእርሱ
ጋር እንደምትሆን
እኔ አላውቀውም እያለ
ሲገዘት
ወዲያው ዶሮ ጮኽ ለሁለተኛ
ጊዜያት
ጴጥሮስ ሲያስታውሰው
ጌታ የተናገረው
በውድቅት ሌሊት ትከዳለህ
ያለው
ዶሮ ሲጮህና ኢየሱስን
ሲያየው
በእርግጥ መክዳቱን ያኔ
ነው ያወቀው።
በቸር ይግጠመን!!!
ኃይሉ ነኝ!! Mar, 2009