ውሻ ይሳምህ !!!
ሰሎሞን
በመኃልየ እንደጻፈው
የፍቅርን ምስጢር እንደገለጸው።
ፍቅር ዜማ ቅኔ እንደተቀኘው
የፍቅርን ኃያልነት ሀሁ ያስተማረው
ፍቅረኛው ለፍቅረኛዋ
ለመከራ ጊዜ ጓደኛዋ
በአፉ መሳም ይሳመኝ
መውደዱን እንዲገልጽልኝ
የፍቅሩ መግለጫ ይህ ነው
ከንፈሬን ግምጥ ሲያደርገው
ነጩ ከንፍሬን ሲያቀላው
እስትንፋሴ ጭልጥ አስኪል
እስትንፋሴ ጭልጥ አስኪል
እስኪያሳጣኝ አቅል
መሳም ነው ምልክቱ
ከኖሩበት በፍቅር ሕይወቱ
አንድ ቀን ግን ያ ዕለት
የተረገመች ለሊት
ጎን ለጎን አብረን ሆነን
በአልጋችን ላይ ተጋድመን
ለሊቱን በሰላም አድረን
ለሊቱን በሰላም አድረን
ጠዋት ከአልጋው ላይ ለመነሳት
ለመሄድ ወደ መስሪያ ቤት
ቅሬን ልሳምሽ ብላት
አላውቅም ያደርግኩትን
በሕልሜ የፈጸምኩትን
በቅዥት ዓለም የሆንኩትን
ያየችው አልገባኝም
ምስጢሩን አልተረዳሁም
እርግማን ይሁን ምርቃት
ውሻ ይሳምህ በማለት
አሰናበተችኝ ወደምሄድበት
ሥራዬን ስሰራ ውዬ
ስኬጅዋሌን አጠቃልዬ
ማታ አመሻሹ ላይ
እኔ ውሻውን ሳላይ
የተረገመ ሶሎግ ውሻ
ሳይታወቅ መነሻውና
መድረሻ
ዘሎ ደረቴ ላይ ተጠመጠመ
እንደ ፍቅረኛው ከንፈሬን
ሳመ
ስሚ አለቅም ብሎ
በግዝት ያገባኝ መስሎ
መከራ ፍዳዬን አሳየቶ
ከከንፈሬ ሙዳ ሥጋ
አንስቶ
በአማልጅ በምልጃ በጩኽት
ሮጦ ገባ ከወደ መጣበት
ጥሩ ፍቅረኛ ያላችሁ
መሳሙን ይሳማችሁ
መግለጫ ነው ለፍቅራችሁ
አትበሉ በምንም ዓይነት
እርግማን ይሁን ምርቃት
ውሻ ይሳምህ ብላችሁ
ሲደርስ ይቆጫል ማለታችሁ
ኃይሉ ነኝ
በቸር ይግጠመን!! 21/08/2014