ማስታወሻ
ከዚህ በታች የሚገኙት ግጥሞች ከ1973 -1975 ባሉት ጊዜያት ከጻፍኳቸው
ሲሆኑ ከማስታወሽዬ ውስጥ ያገኘዋቸው ናቸው።
የምሥራች
ደስታዬን ተካፈሉ እልል በሉ
ዘመድና ወዳጆቼ በሙሉ
አኩርፋኝ የነበረች ጓደኛዬ
መንምኖ የነበረው ተስፋዬ
አንድ ቀን በምሽት
ዘመድ ወዳጆቼ ባሉበት
ላንቀያየም በአንዳች ነገር
ማንም ላያጠፋ ካለን በምድር
ያለፈውን ይቅር ብለን
ለሚቀጥለው በሰላም ለመሆን
ታረቅን ዘመዶቼ
እልል በሉ ወዳጆቼ
የእኔን መጥፎ የማትወደውን
የእሷን ጉድለት የማልሻውን
ጓደኛዬን ወድ እህቴን
አይቻት የማልጠግባትን
ታረቅን እንደ በፊቱ ልንሆን
ኃይሉ ገቢ 1973