በትርህን አንሳው!!!
ሙሴ!! በግብጻውያን ብትናደድ
ከፈርዖን ቤተ መንግሥት
ስትሰደድ
ከግብጽ ተነስተህ በረሃ
ብትወርድ
በዚያ በበረሃ ምድር
በጎችን ስታግድ የአማትህን
የዮቶር
ትይዘው የነበረው ያች ድንቅ
በትር
ጣላት ስትባል ጌታን በማክበር
ስትጥላት እባብ ስታነሳት
በትር
በእግዚኣብሔር ትህዛዝ በጣም
በመደሰት
ይዘሃት የሄድከው ወደፈርዖን
ቤት
የተሰራባትን ድንቅ ታአምራት
ሕዝቡ እግዚኣብሔርን በክብር
ለመቀደስ
ከግብጽ ነጻ ሆኖ ባሕሩ
ዳሩ ሲደርስ
ሕዝቡን ሊያጠፋ ፈርዖን
ሲገሰግስ
ወገኖቼ አትፍሩ እግዜርን
አክብሩ
ፈርዖን በሚያደርገው አትደናበሩ
እግዚኣብሔር ስለእኛ ጠላትን
ይዋጋል
ጸሐይዋ ሳትጠልቅ ድል ለእኛ
ይሆናል
ብለህ በትርህን ወደላይ
ስታነሳ
ፈርዖን ሰምጦነው የሆነው
ሬሳ
በትርህን አንስተህ እጅህን
ስትዘረጋው
የአማሌቅ ሰራዊት በጦር
የሚሸነፈው
በትርህ የታለ? ለማንስ
ሰጠህው?
ሙሴ እንድትነግረኝ ወዴት
አደረግከው ?
ለእኔ ባለአደራ ለኢያሱ
ሰጠውት
ይመልስላችኋል ለእሱም ብትጠይቁት
ኢያሱም ቢሆን ሳለ በሕይወቱ
በኖረበት ዘመን ሲኖር በምድሪቱ
እግዜርን አክብሮ ተስፋን
አስከብሮ
ከሽማግሌዎች ጋር በመግባባት
ኖሮ
በትሩን ሰጥቶአል ለወር
ባለተራው
ሊጠየቅ ሚገባው ባለተራው
ሰው ነው
አደራውን ከኢያሱ የተቀበልከው
ለበትሩ ባለአደራ የሆንከው
በጊዜው በዘመኑ በሕይወት
የምትኖረው
ሲወርድ ሲዋረድ አንተ የተረከብከው
በትርህ ወዴት ነው ያለው?
በበርሃ ስትኖር በጎቹን
ያገድክበት
ወንዝ ስትሻገር ጀልባ የቀዘፍክበት
ጠላት ሲታገልህ ድል የመታህበት
ለነፍሳት መዳኛ ወንጌል
የገልጽክበት
የጠላት ጭንቅላት የፈጠፈጥክበት
ከተማ ስትገባ ወደየት አደርስከው
አንተ ባለአደራ ተስፋህን
አትርሳው
ብዙ ድል ስላለህ አንተ
የምትሰራው
ዛሬም እንደገና በትርህን
አንሳው።
ቸር ይግጠመን!!
ኃይሉ ነኝ!
