Wednesday, October 15, 2014

ዓላማ

                 ዓላማ
በዘጸአት 17፡8-16 ላይ የተመሰረተ ግጥም ነው
አማሌቅ የእግዚኣብሔርን ሕዝብ ሊወጋ
የሕዝቡን እምነት ሊያናጋ
ወደ ራፊድ ምድር ቢጠጋ
ነጻ የወጣውን ሕዝብ ሊያስገብር
እንዳይወርስ የተጥራበትን ምድር
እግዚኣብሔር ተመልክቶ የልቡን ክፋት
አማሌቅ ሕዝቡን ከማጥፋቱ በፊት 
እግዚኣብሔር ሙሴን ጠርቶት
እንደዚህ ብሎ አለው
የአማሌቅን ዝክር አሳየዋለሁ
ለዘላለም ከምድረ ገጽ አጠፋዋለሁ
ለሌሎች መቀጣጫ አደርገዋለሁ
ይህንን የእኔን ጦርነት ተዋጋ
ድል ያንተ ነው አትዘናጋ
ሙሴ ይህንን ዜና ሲሰማ
አመነ እንደሚደመሰስ የጠላት አድማ
ሙሴ አንግቦ የእግዚኣብሔር በትሩን
ከፍ አድርጎ የሚያውለበልበውን
የተጠራበት አመራሩን
ወጣ ወደ ኮረብታ ይዞ አቅጣጫውን
ረዳት አድርጎ ሖርና አሮንን
ኢያሱም ለጦርነት የሚያስፈልጉትን
ወጣት ጀግና የሆኑትን
የእግዚኣብሔር ጦርነት የሚዋጉትን
ወረደ ወደራፊድ ሊመራ ጦርነቱን
ሊበቀላቸው አማሌቃያንን
አሮንና ሐር የሙሴን እጅ በመሸከም
የዛለው ጉልበቱ እንዳይደክም
እያሱ ጦርነቱን እንዲያሸንፍ
ሰራዊቱ በአንድነት እንዲሰለፍ
አማሌቅ ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ
የእግዚኣብሔር ሕዝብ እንዳይከፋ
ነበረ ሰንደቅ ዓላማቸው
እግዚኣብሔር የሰጣቸው
ከግቡ ያደረሳቸው
ዛሬም እኛ በደረስንበት ዘመን
እግዚኣብሔር የሰጠን ወንጌላችን
የሰላም መጫሚያችን
በአንድነት በሕብረት ተያይዘን
የሰይጣንን ክንድ ሰባብረን
ሥራውን አፈራርሰን
የእግዚኣብሔርን መንግስት አድረሰን
ሕዝቡን ነጻ አውጥተን 
ማየት  ነው ዓላማችን
ወንጌል ለሕዝብ ማድረሳችን
በቸር ይግጠመን!!
ኃይሉ ነኝ Oct 15/2014




No comments:

Post a Comment