Sunday, April 21, 2013

አጥብቃችሁ ያዙ


አጥብቃችሁ ያዙ
እግዜር የሚያከብሩ ለእርሱ ያደሩ
በቤት በኑሮአቸው ጌታን የሚያከብሩ
አንድ ምዕራፍ ሲባሉ የሚሄዱ አስር
በመስጠት በመርዳት ስለጌታ ፍቅር
እግዚኣብሔር የሰጠው እግዚኣብሔር ያመጣት
እንዴት ታድለዋል ርብቃ ያለችበት
እግዚኣብሔር ሰጥቶአችሁ ርብቃ ያላችሁ
በቤት አደባባይ ክብር የምትሰጣችሁ
ወደቤት ስትሄዱ ደክሞአችሁ ከሥራ
ንገርህን አይታ ለአንተ የምትራራ
በርህራሄነትዋ አንተን የምታኮራ
በረከት ካሻችሁ ከፊት ለፊታችሁ
አጥብቃችሁ ያዙ ምክር እየሰማችሁ
                 በቸር ይግጠመን!!!
                ኃይሉ ነኝ! 2006

No comments:

Post a Comment