Wednesday, May 24, 2017

Abba Jifar palace(የኣባ ጂፋር ቤተ መንግሥት)

Friday, March 4, 2016

እናት
ደስታ ፍቅር ባለበት
ወይም መከራና ስደት
እናት ለልጅዋ የማይሰለቻት
ሁልጊዜም በሁሉም ቦታ አንድ ናት
ልጅዋ ሲታመምባት
ሲከፋው እየከፋት
ሲደሰት እያስደሰታት
በምጥ ታማ እየጨነቃት
እሷ እየራባት እየጠማት
ልጅዋን የምትመግብ እናት ናት
            ኃይሉ ነኝ
March 1/2016