Friday, March 14, 2014

ገንዘብ ወይስ ሕይወት!!??


    ገንዘብ ወይስ ሕይወት?

እንግዲህ ከሁሉ በላይ ሕይወታችሁ የክርስቶስን ወንጌል

የሚያስመሰግን ይሁን             ፊልጵስዮስ 1፡27


ምኞቴ ፀሎቴ ጌታን ማገልገል ነው

የጠፋው ወገኔ ወንጌል እንዲደርሰው

እኔ ያገኘሁትን እሱም እንዲቀምሰው

ነበረ ሃሳቡ ወንጌላዊ ሳለ

እቅዱ ተቀይሮ እንደዚህ ደግሞ አለ

ረጅም ዓመታት በጌታ ቤት ውስጥ ነኝ

በወንጌላዊነትም ብዙ ዘመን ሆነኝ

በረሃ ቆንጥሩን ዱር ገደሉን አየሁ

በነዚያ ጉዞዬ ወንጌልን አደረስሁ

አሁን ግን ሳስበው ቃሉን ተምሬአለሁ

ከቴዎሌጂ ኮሌጅ ድግሪዬን ይዣለሁ

በአሰባበክ ይዘት በደንብ ተክኛለሁ

በፈተናም ቢሆን ውጤት አምጥቻለሁ

በሄድኩበት ሁሉ ታዋቂ ሆኛለሁ

ወንጌላዊ መሆን ምንም ጥቅም የለው

የሚሰፈርልኝም በጣሙን ትንሽ ነው

ሕዝቡ ከመረጠኝ ሕዝቡ ካፈቀረኝ

ለወጣት ለሴቶች ራዕይ ስላለኝ

የቤቱን ጉባኤ እኔ የምመራው

ወደ እሁድ ጉባኤ አሁን ብቀይረው

በሌድ ፓስተርነት ጉባኤውን እንድመራው

ለጠቅላላ ጉባኤ ይህንን መንገር ነው

ፓስተር መሆኑ ነው ለእኔ የሚሻለው

በተለያየ ምክንያት የሚሰበሰበው

ሕንፃ ለማሰራት ቤትን ለማስገንባት

ጠበበ እናስፋው እንስራ በማለት

አስራትና መባ ከሕዝብ የሚዋጣው

ደጋግ ሕዝብ ደግሞ እጁ የሚዘረጋው

ከመጠን ያለፈ ብዙ ገቢ ስላለው

በእነዚህ ሁሉ ላይ እኔ ስለማዘው

ከወንጌላዊነት በጣም የተሻለ ነው

ቢጠፋ ቢጠፋ በደመወዝ እኖራለሁ

እንደዚህ በማለት ሁሌ የምታስበው

የአምላክ ቤት አፍርሶ እገነባለሁ ማለት

በጤና አይደለም እንዳይመጣ መቅሰፍት

ተጠንቀቅ ወንድሜ በጣም አስብበት

ምርጫ የትኛው ነው ገንዘብ ወይስ ሕይወት

               በቸር ይግጠመን!!!

                 ኃይሉ ነኝ!      


በእግርህ ሥር!


                             በእግርህ ሥር

                     ለማወቅ ለመማር ለመረዳት

                      ያንተን ታላቅነትና ምሕረት

                      የአሸናፊነትህን እውነት

                       ሚስጢሩን ሁሉ ጠንቅቃ

                        አምላክነትህን አውቃ

                        ማርያም እንዳደረገችው

                         በእግርህ ሥር እንደተቀመጠችው

                         እኔም ጌታ ሆይ በተራዬ

                          አንተ ብቻ ነህ አምባዬ

                          ስለዚህ አውቃለሁ ብዬ ስከንፍ

                          በጠላት እንዳልጠለፍ

                          ተምሬ ከአፍህ ቃል እንዳተርፍ

                          በመስቀልህ ሥር ልሁን ልረፍ

                           አንተን ሁልጊዜም እንዳከብር

                           ልቀመጥ ጌታ በእግር ሥር።

                                         ኃይሉ ነኝ!!

በሐዲዱ ላይ ነኝ!!


በሐዲዱ ላይ ነኝ!!!

ጨቅላ እንደነበርኩ ያኔ በእምነቴ

ሁኔታው ቢከብደኝ ብዝል በሕይወቴ

ጌታ አንዲህ አለኝ

መዝለቅ ነው የምትሻው ለዘላለም ሕይወት

አባት እናቶችህ ወደተሻገሩበት

ከቅዱስን ጋራ በቤቴ ለመኖር

መኖር ለዘላለም በቅዱሳን መንደር

ቅዱስ ቅዱስ ብለህ እኔኑን ለማክበር

እንደመናኝ ተጓዝ ቀጥለው መንገዱን

ወዲህ ወዲያ ሳትል ተከተል ሐዲዱን

ትደርስበታለህ መልካም የሆነውን

የጌታ ቃል ይዤ የተነገረውን

መከራ ሲመጣ ከሐዲድ የሚያስወጣ

ጠራርጎ የሚወስደው የዓለማችን ጣጣ

ያንን ሁሉ ችዬ በአምላኬ ብርታት

ችግሩ ሲመጣ ጌታን እየተማጠንኩት

ከሐዲዱ ሳልወጣ ሁሉን ነገር ችዬ

በሐዲዱ ላይ ነኝ ዛሬም ከጌታዬ

         ኃይሉ ነኝ

         Oct 20/2013hailuelalagebihailuelalagebigmailcom-marta.blogspot.com